ግዮን የእርቀ ሰላምና ልማት ማህበር ሃገር በቀል የግጭት አፈታት መንገዶችን በመጠቀም ግጭቶችን የመለየት፤ የሃገር ሽማግሌዎችን ማደረራጀትና ግጭቶችን እንዲፈቱ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ባደረጋቸው ተግባራት በአምባ ጊዎርጊስና አካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶችን መፍታት ተችሏል። በእነዚህ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፎ የነበራቸው ከ10 በላይ የተጋጩ ሰዎች እርቅ ፈፅመው ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለሳቸውም ተገልጧል። “ደም በደም አይደርቅም”
Read Moreግዮን የእርቀ ሰላምና ልማት ማህበር “የእርቅ ሳምንት” በሚል የሁለት ወራት መርሃግብር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሳንጃ ከተማ አስጀመረ። ይህ ፕሮግራም በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት የሚደረግ ሲሆን በአካባቢው ካለው የችግሩ ስፋት አኳያ በተመረጡ አካባቢዎች ለተከታታይ 2 ወራት የሚከናወን ነው። በመርሃ ግብሩ የሚከናወነውን የእርቅ ተግባር በተመለከተ፥ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ•ም በጎ ፈቃደኞች በማዕከላዊ ጎንደር […]
Read More