ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር በጎንደር ከተማ ስድስቱ ክ/ከተሞች ለተወጣጡ ከ60 በላይ ስመጥር አባቶች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና እናቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በኦሎምፒክ ሆቴል መስጠት ችሏል። ሰላማችሁ የበዛ ይሁን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2013 ዓ.ም
Read Moreእኒሁ አባት አደገ አመራ ይባላሉ። መኖሪያቸው ምዕራብ በለሳ አስዋጋሪ ቀበሌ ሲሆን ሙሉ ጊዜያቸውን ሽምግልና በተደገሰበት ዛፍ ፅላሎት ስር አይታጡም። አቶ አደገ ሽምግልናን በመጠቀም ብዙ የጥልና ክርክር ተቃርኖን በማስወገድ ዘለግ ያለ አበርክቶ አላቸው። በተለይ በጥቁር ደም (ደም መቃባት) ምድረ በለሴው ሲታወክ የተረበሸ ወገናቸውን ለመታደግ የሚቀድማቸው አልተገኘም። እንደሚታወቀው በለሳ ጀግንነቱ አርበኝነቱ የሚያጠያይቅ ባይሆንም በርስ በርስ መዳማቱ ላይ […]
Read Moreራያ በህግ አምላክ ከምትለው ‘በዘወልድ አምላክ’ ብትለው ያነሳውን ይጥላል ለጠብ የተጋበዘበትን አጋጣሚ እርግፍ አድርጎ ይተዋል የሚባለው እሙን ነው። ከመደበኛው ፍርድ ቤት እጅግ በቀለጠፈና በተሻለ መንገድ ግጭቶችን የመፍታትም ሆነ ባለመብትነትን የማረጋገጥ ልዩ አቅም ያለው የራያ ቆቦው “የዘወልድ ሽምግልና”። ራያዎች በዕፁብ ተረካቸው አንድ ትዕውፊትን ያዘክራሉ። ሰንየ ሰገድ፣ ክፍሎ፣ መዘርድ እና ዘወልድ የሚባሉ አራት ወንድማማቾች ስም የሚጠራ የወንዝ […]
Read Moreበአንድ ወቅት የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የወንድም ልጅና የእቴጌ ዘውዲቱ ባለቤት የነበሩት ራስ ጉግሳ ወሌ ደብረ ታቦር ላይ ሸንጎ ቆይተው ሲነሱ አንድ ዛፍ ስር አንዳች ክስተትን አስተዋሉ። እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ ነው ግራሩ ስር የተቀመጡት? ሲሉ አብረው ያሉትን አሽከሮቻቸውን ጠየቁ። እነርሱም እነዚህማ የተቀደደን ቤት እየሰፉ ፥ የተጣሉትን እያስተረቁ ደምን እያደረቁ ነው አሏቸው። ይህንን በጎ ግብር ሲፈፅሙ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በወገራ በተለያየ መንገድ ግጭት ውስጥ የነበሩ ከ150 በላይ ግለሰቦችን ያካተተ የእርቀ ሰላም ፕሮግራም አካሄደ
በአምባጊዮርጊስ ከተማ በደብረ ጸሐይ መድሐኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተገኙት የግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) አመራሮች በመሩት የእርቀ ሰላም ጥሪ መሰረት 150 ግለሰቦች በተለያየ መንገድ ቅር የተሰኙኙ ሰዎችን በራሳቸው ፈቃድ ተነስተው ይቅር ማባባል ችለዋል።ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ህዳር 14/3/2012 ዓ/ም
Read Moreየግዮን ወገራ ቡደን ወደ ወይላሆ ደብረ ማርያም በማቅናት ህዝቡን በማሰባሰብና በማስተማር በ30 ሰዎች መካከል የነበረውን ጥልና ግጭት በዕርቅ አስወግደዋል። ልዑክ በድኑ ግዮናዊ ትምህርት በመስጠትም ቀበሌውን የሚወክሉ ግዮናዊ አባቶችን አቋቁመዋል። ግዮን ዘወገራ ተባረኩልን!! ጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)
Read Moreማህበራችን በሁለት ወረዳዎች ማለትም በወገራና ምዕራብ ደምቢያ ተግባራትን ፈፀመ። ከጎንደር ወደ ወገራ አምባጊዮርጊስ ያቀናው ግዮናዊ ልዑክ ከግዮን አባቶችና አመቻች ወጣቶች ጋር ተወያይቶ ከዚያም ከወገራ ወረዳ ሶስት የመንግስት አመራሮች ጋር ምክክር አደርጎ ተመልሷል። በምዕራብ በለሳ እዚያው አርባያ በሚገኙ ግዮናዊያን ስራ አስፈፃሚዎች የወረዳው አስተዳደር ለቀበሌ አመራሮችና ለሌሎች የፀጥታ ባለድርሻ አካላቶች ባዘጋጀው መድረክ ላይ ግዮናዊ ተልዕኮን ለታዳሚው ማስተላለፍ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)በጎንደር ከተማ በአዲስ ዓለም፣ በልደታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በገብርኤል ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያሻቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ተማሪዎቹ ከተለያዩ ት/ቤቶች እንዲሁም ከተለያዩ የትምህርት ደረጃ የተወጣጡ ሲሆን ማህበሩ በግዮን አምባሳደሮች ልዩ ጥረት ከራሱ ከማህበረሰቡ በጎ ፈቃደኛ እጅ የሰበሰበውን ደብተርና እስክርቢቶ በተጠና መልኩ ለታዳጊዎቹ አከፋፍሏል። መስከረም 15/2012 ዓ.ም
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በርስ በርስ ግድያ አቅሉን እንዲያጣ ጣሊያን ተብትቦት የሄደውን የጥቁር ደም ጥቁር ገመድ ለመበጣጠስ አቅሙ በፈቀደው ልክ ደፋ ቀና እያለ የሚገኝ ተቋም ነው። ማህበሩ በሰሞናት የሰላም አምባሳደሮቹን ፈጥሯል። ታዳጊዎቹ ከተለያዩ ከተማችን ከሚገኙ አማተር የጥበብ ደጆች የተወጣጡ ሲሆን በትላንትናው ዕለት በጎንደር ሀይሌ ሪዞርት የሰላም አምባሳደርነት ስልጠና ማለትም የዕርቀ ሰላምን የማይተመን ዋጋ […]
Read Moreልዑኩ በዚሁ ወረዳ በሰንደባ ቀበሌ የፀጥታ ጉዳይ በነበረው ልዩ መድረክ ተገኝቶ ስለ ጥቁር ደም አስከፊነት እንዲሁም ለቅሶ ላይ ስለሚተኮስ ጥይት ሰፊ ግዮናዊ ግንዛቤ አስጨብጠዋል። የደምቢያ ማሩ ቀመስ ቆይታችን የግዮን ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት ከግዮን የወረዳው አባቶችና አመቻች ወጣቶች ጋር የጋራ ውይይት አድርጎ የወረዳው ፀጥታ አስተዳደር ባዘጋጀው መድረክ ላይም ተጋብዞ ግዮናዊ መልዕክት አስተላልፏል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት […]
Read More