የሙርሀንገብ ዳኝነት እና በለሳ—ነባር ይትባህሉ ወደ ፊት ሊመጣ የሚገባዉ ስርዓት

በለሳ እና አካባቢዉን ከእርስ በርስ መዳማት ጋር በተያያዘ ያለውን ስም ለመፋቅና አካባቢዉን ከስጋት አርነት ለማውጣት ከተጉት መሀል የሙርሀንገብ ኪዳነ ምህረት ፍርድ ሸንጎዎች አንዱ ናቸው። በሙርሀንገብ ሸንጎ አያሌ የግጭት መዝገቦች ተዘግተዋል። ደም የተቃቡ በሽምግልና ቋንቋ ተግባብተው ደም አድርቀዋል። በዚህ የሙርሀንገብ ዳኝነት ወጥ የሆነና ሁሉም ማህበረሰብ ንቁ ሱታፌ ያደረገበት የማስቻያ አንቀፆች ተቀምጦላቸዋል። ለአብነት ምርሀንገቦች የጥቁርና ቀይ ደምን […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በሁለት የጎንደር የገጠር ቀበሌዎች በመገኘት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኙ አጀንዳዎች ዙሪያ ማኀበረሰብ አቀፍ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) አስተባባሪነት ግንቦት 14/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በአባ እንጢንዎስና በብላጅግ ድባርቃ ቀበሌ በመገኘት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኙ አጀንዳዎች ዙሪያ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት በጥልቅ ተመክሯል። የምክክሩ ዓብይ ጉዳይም ከአሁን በፊት በአማራና ቅማንት ወንድማማች ማኅበረሰቦች መካከል እኩያን ቀስቅሰውት በነበረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ እንግልት የተዳረጉ ወገኖችን በማቀራረብ […]

Read More

ማህበሩ በላይ አርማጫሆ ወረዳ ጎንደሮች ማርያም ቀበሌ በመገኘት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኙ አጀንዳዎች ዙሪያ ማኀበረሰብ አቀፍ ውይይት አካሄደ

በግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) አስተባባሪነት ግንቦት 14/2014 ዓ.ም በላይ አርማጫሆ ወረዳ አስተዳደር ጎንደሮች ማርያም ቀበሌ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኙ አጀንዳዎች ዙሪያ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት በጥልቅ ተመክሯል። የምክክሩ ዓብይ ጉዳይም ከአሁን በፊት በአማራና ቅማንት ወንድማማች ማኅበረሰቦች መካከል እኩያን ቀስቅሰውት በነበረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ እንግልት የተዳረጉ ወገኖችን በማቀራረብ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኝ ጉዳይ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር ከዲኤክሲስ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ግምታቸው ከ180,000 ብር በላይ የሆነ የቢሮ ቁሳዊ ድጋፍ ተበረከተለት

ማኅበራችን ከዩስኤድ ጋር በመስራት የሚታወቀው ዲኤክሲስ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ግምታቸው ከ180,000 ብር በላይ የሚሆኑ የቢሮ ግብዓቶችን ለማኅበራችን አበርክቷል። ግብዓቶቹም ደረጃቸውን የጠበቁ ላፕቶፖች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተርና ሌሎች ናቸው። የተበረከቱት ግብዓቶች ባለፉት ወራት በድርጅታቸው ኦቲአይ አጋርነት በሰራነው “ወጣቶችን ከሀይማኖት አባቶች ጋር የማገናኘት የውይይት ማዕቀፍ” በብቁ አተገባበራችን እንደሆነ በመጥቀስ ከበርካታ አጋር ሲቪክ ማኅበራት ጋር በንፃሬ የተሻለ የስራ አፈፃፀም በማስመዝገባችን እንደተበረከተልን […]

Read More

በመተባበር በሰላም አብሮ የመኖር ባህል ለማሳደግ የሚያስቾል የልምድ ልውውጥና የእርስ በርዕስ የመማማር አውደ ጥናት በጎንደር ከተማ ተካሄደ

ያለ መግባባት ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችለውን ባህላዊ የሽምግልና የዳኝነት ስርዓት ማጠናከር ይገባል ተባለ። የወሎ ዩኒበርስቲ ፣ጊዎን የዕርቀ ሰላምና ልማት የበጎ አድራጎት ማህበር፣ፕሮ ዲቨሎፕመንት ኔት ወርክና ትራንዚሽን ኢኒሽቲቭ የተባለ የአሜሪካን ተራዶ ድርጅቶች በመተባበር በሰላም አብሮ የመኖር ባህል ለማሳደግ የሚያስቾል የልምድ ልውውጥና የእርስ በርዕስ የመማማር አውደ ጥናት በጎንደር ከተማ ተካሒዷል። በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የጊዎን ዕርቀ […]

Read More

ማኅበራችን መንገዘዝ ከተሰኘ የኪነጥበብ ድርጅት ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ 

አዲስ አበባ የሚገኘው መገዘዝ የኪነጥበብ ድርጅት በታዋቂው አርቲስት አንዱዓለም አባተ (የአፀደ ልጅ) የተመሰረተና የሚመራ ሲሆን በሰላም ዕሴት ግንባታና ግጭት መከላከል ላይ ያተኮረ ስራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች መክረናል። በኪነጥበብ መሣሪያነት የግጭት ቅድመ መከላከል ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ ለመስራት የጋራ መግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding) ተፈራርመናል። ሰላማችሁ የበዛ ይሁን ግዮን ሰላምና ልማት ማህበር ታህሳስ፣ 2014 ዓ.ም

Read More

የማኅበራችን አባላትና ደጋፊዎች ደም ለገሱ

የማኅበራችን አባላትና ደጋፊዎች በጎንደር ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ በመገኘት በዛሬው ዕለት ማለዳ 3:00 ጀምሮ የደም ልገሳ ፕሮግራም ማካሄድ ችለዋል። አባላቶቻችንና ደጋፊዎቻችን እናመሰግናለን። ሰላማችሁ የበዛ ይሁን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሕዳር፣ 2014 ዓ.ም

Read More

ማኅበራችን “ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ የአራት ቀናት የውይይት መድረክ አካሄደ

ማኅበራችን ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በአይከል ከተማ እና በጎንደር ከተማ ዙሪያ ቀበሌዎች “ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት” በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ አካሄደ። ይህ  የውይይት መድረክ ከጥቅምት 15-18/2014 ዓ/ም የተደረገ ሲሆን ከጎንደር ከተማና አይከል ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶች፤የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በኤጂ ሆቴልና ሄርፋዚ ሪዞርት በአራት የመወያያ አዳራሾች በተለያዩ አጀንዳዎች ሲወያዩ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት በሚል የውይይት መድረክ አዘጋጀ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር “በአይከል ከተማ እና በጎንደር ከተማ ዙሪያ ቀበሌዎች ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት በሚል የውይይት መድረክ” ለማዘጋጀት ከአመቻች ወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ሸምጋይ አባቶች ጋር ጥቅምት 12 እና 13 2014 ዓ/ም የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ ኤጂ ሆቴል ማካሄድ ችሏል። ከጎንደር ከተማና አይከል ከተማ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአይከልና ትክል ድንጋይ ከተሞች መድረኮች እንዲፈጠሩ ትልቅ ሚና ተጫወተ

የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔ አቶ አዳም ፈራዕና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት የሰላም መድረክ ማኅበራችን ግዮን ትልቅ ድርሻን ወስዷል። በተለይም የቅማንት ማኅበረሰብ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የአሰላለፍ ውግንናው ከመላው ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር መሆኑን በተግባር ያሳየበት ልዩ ታሪካዊ መድረክ እንደነበር ማስተዋል ተችሏል። ሰላማችሁ የበዛ ይሁን!! ግዮን ሰላምና ልማት ማህበር ነሀሴ፣2013 ዓ.ም

Read More