ግዮን የእርቀ ሰላምና ልማት ማህበር የህዝብ ለህዝብ መድረኮችን አካሄደ

በላይ አርማጭሆ ወረዳ ጎንደሮች ማርያም ቀበሌ እና የጎንደር ከተማ አጎራባች ቀበሌ በሆነው የብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ የላይ አርማጭሆ ወረዳ እና የጎንደር ከተማ የፀጥታ አመራሮች፣የማህበራችን አባላት እና የቀበሌዎች ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ጥር 03/2015 ዓ/ም የህዝብ ለህዝብ መድረክ ተካሂዷል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጥር ፣ 2015 ዓ.ም

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአባ እንጦኒዮስ ቀበሌ በሚገኘው የአባ እንጦኒዮስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ዙሪያ የሰላም አስተምህሮ አካሄደ

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) የማህበሩ አባላት፣የቀበሌው አመራሮች እና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት የአባ እንጦኒዮስ ትምህርት ቤት በመገኘት የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ስለሚጠቅበት እና በማህበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ተማሪዎች አውንታዊ ሚናቸውን በሚወጡበት ዙሪያ የሰላም አስተምህሮ ሰጥቷል። በዚህ ወቅትም ተማሪዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለፁ ሲሆን ማህበራችን በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የተወጣውን ሚናም አወድሰዋል። በወቅቱ የነበሩ […]

Read More

ወገራና ባህላዊ የፍትህ መስጫው-ዶሮ ማጣፈጫ (ሌላዉ ወደፊት ሊመጣ የሚገባውና የተደበቀዉ እሴት)

የዶሮ ማጣፈጫ ባህላዊ ፍትህ በወገራ ወረዳ ኖራ ፃድቃን ልዩ ስሟ ዶሮ ማጣፈጫ በሚሏት ኮረብታማ ስፍራ ይከወን የነበርና ሙሉ ስሜን በጌምድር በፈረስ በበቅሎ ተጉዞ ለይግባኝ አቤት ይልበት የነበር የሁለቱ ጠቅላይ ግዛቶች ማዕከላዊ መገናኛ ነጥብም ነበረች። በዚህ የዶሮ ማጣፈጫ የይግባኝ ዳኝነት ጉልበት እንዲያገኝ ስመ ማህተም ከነበራቸው ሰዎች መሀል ብላታ ቦጋለ፣ ግራዝማች አለሙ፣ ፊታውራሪ ከበደ ጀምበሬ፣ ብላታ ላቀው፣ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ የእርቅ መርሀ-ግብር አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምከንያት የላሉ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ፣በአካባቢው የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት፣ማህበራዊ ተቋማትን ስራ ለማስጀመር እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ የእርቅ መርሀ-ግብር አካሄደ። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር በቅማንት እና አማራ […]

Read More

ጃንተከል፣ ጎንደር እና ዕርቅ ቤት

ጎንደር ከተማ በሀገራችን ታሪክ 200 ዓመታትን በማዕከልነት ቆማ የአፍሪቃ ቀንድ የስልጣኔ መናገሻ ነበረች፡፡ ጎንደር የስጋና የነፍስ ውህድ በመሆን ሰላምና ፍቅር ከምትሰብክባቸው አጸዶቿ መሀል የጃንተከል ሽምግልና እንዲሁም የዕርቅ ቀየዋ ዕርቅ ቤት ይገኝበታል፡፡ የጃንተከል ባህላዊ ፍትህ “ጃን ማለት ንጉስ ነው ተከል ደግሞ መትከል የቀለሱት ጎጆ ሁለቱ ተጋብተው ይሆናል የጸና ንጉስ የተከለው (ፍሬዘር እንግዳ፣ 2010) አጤ ፋሲል ወደ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ቀበሌ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ስለሚቋቋሙበት እና በአካባቢው ዘላቂ ሰላም በሚሰፍንበት ዙሪያ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት ውይይት አካሄደ።

ግዮን ሰላምና ልማት ማኅበር በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ቀበሌ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ከአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ፤ በአካባቢው የቅማንት እና አማራ ወገኖች መካከል የነበረው አብሮነት ወደ ድሮው ግንኙነት ስለሚመለስበት እና በአጠቃላይ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ስለሚሰፍንበት መንገድ ጥልቅ ውይይት አድርጓል። በውይይቱም የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ማለደ፤ የወረዳው የአስተዳደር ፀጥታ ኃላፊ አቶ […]

Read More

የስጋት አየር ከቧት ከወገራ ወረዳ እስከ ጎንደር ከተማ ዘልቃ የምትገባው የኩዳድ መንገድ ክፍት እንድትሆን መግባባት ተፈጠረ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ከተማ ፋሲል ክ/ከተማ ስር የሚገኙ ሳይሳ ሳቢያና ድባ ደፈጫ፤ በላይ አርማጭሆ የባንብሎ ጭጋሳ ቀበሌ፤ በጎንደር ዙሪያ ስሆር ጉልቶች ቀበሌ የወረዳና ቀበሌ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት፣ የሕዝብ እንደራሴዎች በንቃት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በምክክሩም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች ተጠናከረው እንዲቀጥሉ የሚያስችሉ ተከታታይ የማሕበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን በቀጣይነት ለማካሄድ፤በሁሉም ቀበሌዎች በራ ጠፋ የሚሉ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በድባ አቦ መንደር በመገኘት የቀበሌ አመራሮች በተገኙበት በዘላቂ ሰላም ዙሪያ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም በድባ አቦ መንደር በመገኘት ፍሬያማ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይቱም ተሳታፊዎች በአካባቢው ተፈጥሮ ከነበረው ችግር በኃላ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም

Read More

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጎንደርና አካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት የሚጠይቁ አካባቢዎችን በመለየት የሰላም ግንባታ በድባ ደፈጫ ቀበሌ አካሄደ

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጎንደርና አካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት የሚጠይቁ አካባቢዎችን በመለየት የሰላም ግንባታ ስራውን የቀጠለ ሲሆን በድባ ደፈጫ ቀበሌ የነበሩ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ቀደመ ኑባሬያቸው እንዲመለሱ እና እንዲጠናክሩ ያለመ ዝግጅት አድርጓል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ዙሪያ ግጭት ተፈጥሮባቸው ከነበሩ ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ድባ ደፈጫ ቀበሌ የአካባቢውን […]

Read More

በጎንደርና አካባቢው የህዝባችንን አብሮነትና ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ ተግባራት ቀጥለዋል

በቆላድባ ከተማ እና በአይከል ከተማ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሂዷል። በቆላድባ ከተማ አዘጋጅነት የሚካሄደውን የወዳችነት የእግር ኳስ ጨዋታ ለማካሄድ የአይከል ከተማ የእግር ኳስ ቡድንን የቆላድባ ከተማ መህበረሰብ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል። እነዚህን እና መሰል ተግባራትን ልንደግፍ ይገባል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም

Read More