Category: አማርኛ ዜና

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት በሚል የውይይት መድረክ አዘጋጀ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር “በአይከል ከተማ እና በጎንደር ከተማ ዙሪያ ቀበሌዎች ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት በሚል የውይይት መድረክ” ለማዘጋጀት ከአመቻች ወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ሸምጋይ አባቶች ጋር ጥቅምት 12 እና 13 2014 ዓ/ም የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ ኤጂ ሆቴል ማካሄድ ችሏል። ከጎንደር ከተማና አይከል ከተማ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአይከልና ትክል ድንጋይ ከተሞች መድረኮች እንዲፈጠሩ ትልቅ ሚና ተጫወተ

የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔ አቶ አዳም ፈራዕና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት የሰላም መድረክ ማኅበራችን ግዮን ትልቅ ድርሻን ወስዷል። በተለይም የቅማንት ማኅበረሰብ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የአሰላለፍ ውግንናው ከመላው ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር መሆኑን በተግባር ያሳየበት ልዩ ታሪካዊ መድረክ እንደነበር ማስተዋል ተችሏል። ሰላማችሁ የበዛ ይሁን!! ግዮን ሰላምና ልማት ማህበር ነሀሴ፣2013 ዓ.ም

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ለአባሎቹ  የአቅም ግንባታ ስልጠና ስጠ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር በጎንደር ከተማ ስድስቱ ክ/ከተሞች ለተወጣጡ ከ60 በላይ ስመጥር አባቶች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና እናቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በኦሎምፒክ ሆቴል   መስጠት ችሏል። ሰላማችሁ የበዛ ይሁን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2013 ዓ.ም

Read More

በሽምግልና ምክንያት ልጃቸውን አፈር ማልበስ ያልቻሉት ርቱዕ አባት

እኒሁ አባት አደገ አመራ ይባላሉ። መኖሪያቸው ምዕራብ በለሳ አስዋጋሪ ቀበሌ ሲሆን ሙሉ ጊዜያቸውን ሽምግልና በተደገሰበት ዛፍ ፅላሎት ስር አይታጡም። አቶ አደገ ሽምግልናን በመጠቀም ብዙ የጥልና ክርክር ተቃርኖን በማስወገድ ዘለግ ያለ አበርክቶ አላቸው። በተለይ በጥቁር ደም (ደም መቃባት) ምድረ በለሴው ሲታወክ የተረበሸ ወገናቸውን ለመታደግ የሚቀድማቸው አልተገኘም። እንደሚታወቀው በለሳ ጀግንነቱ አርበኝነቱ የሚያጠያይቅ ባይሆንም በርስ በርስ መዳማቱ ላይ […]

Read More

የቀለጠፈ ዳኝነት በራያ ዘወልድ ሸምጋይነት

ራያ በህግ አምላክ ከምትለው ‘በዘወልድ አምላክ’ ብትለው ያነሳውን ይጥላል ለጠብ የተጋበዘበትን አጋጣሚ እርግፍ አድርጎ ይተዋል የሚባለው እሙን ነው። ከመደበኛው ፍርድ ቤት እጅግ በቀለጠፈና በተሻለ መንገድ ግጭቶችን የመፍታትም ሆነ ባለመብትነትን የማረጋገጥ ልዩ አቅም ያለው የራያ ቆቦው “የዘወልድ ሽምግልና”። ራያዎች በዕፁብ ተረካቸው አንድ ትዕውፊትን ያዘክራሉ። ሰንየ ሰገድ፣ ክፍሎ፣ መዘርድ እና ዘወልድ የሚባሉ አራት ወንድማማቾች ስም የሚጠራ የወንዝ […]

Read More

አግቦ ሽምግልና!

በአንድ ወቅት የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የወንድም ልጅና የእቴጌ ዘውዲቱ ባለቤት የነበሩት ራስ ጉግሳ ወሌ ደብረ ታቦር ላይ ሸንጎ ቆይተው ሲነሱ አንድ ዛፍ ስር አንዳች ክስተትን አስተዋሉ። እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ ነው ግራሩ ስር የተቀመጡት? ሲሉ አብረው ያሉትን አሽከሮቻቸውን ጠየቁ። እነርሱም እነዚህማ የተቀደደን ቤት እየሰፉ ፥ የተጣሉትን እያስተረቁ ደምን እያደረቁ ነው አሏቸው። ይህንን በጎ ግብር ሲፈፅሙ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በወገራ በተለያየ መንገድ ግጭት ውስጥ የነበሩ ከ150 በላይ ግለሰቦችን ያካተተ የእርቀ ሰላም ፕሮግራም አካሄደ

በአምባጊዮርጊስ ከተማ በደብረ ጸሐይ መድሐኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተገኙት የግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) አመራሮች በመሩት የእርቀ ሰላም  ጥሪ መሰረት 150 ግለሰቦች በተለያየ መንገድ ቅር የተሰኙኙ ሰዎችን በራሳቸው ፈቃድ ተነስተው ይቅር ማባባል ችለዋል።ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ህዳር 14/3/2012 ዓ/ም

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በወገራ በ30 ሰዎች መካከል የነበረውን ጥልና ግጭት በዕርቅ ፈታ

የግዮን ወገራ ቡደን ወደ ወይላሆ ደብረ ማርያም በማቅናት ህዝቡን በማሰባሰብና በማስተማር በ30 ሰዎች መካከል የነበረውን ጥልና ግጭት በዕርቅ አስወግደዋል። ልዑክ በድኑ ግዮናዊ ትምህርት በመስጠትም ቀበሌውን የሚወክሉ ግዮናዊ አባቶችን አቋቁመዋል። ግዮን ዘወገራ ተባረኩልን!! ጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በሁለት ወረዳዎች ከሚገኙ የመንግስት አመራሮች ጋር በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ምክክር አደረገ

ማህበራችን በሁለት ወረዳዎች ማለትም በወገራና ምዕራብ ደምቢያ ተግባራትን ፈፀመ። ከጎንደር ወደ ወገራ አምባጊዮርጊስ ያቀናው ግዮናዊ ልዑክ ከግዮን አባቶችና አመቻች ወጣቶች ጋር ተወያይቶ ከዚያም ከወገራ ወረዳ ሶስት የመንግስት አመራሮች ጋር ምክክር አደርጎ ተመልሷል። በምዕራብ በለሳ እዚያው አርባያ በሚገኙ ግዮናዊያን ስራ አስፈፃሚዎች የወረዳው አስተዳደር ለቀበሌ አመራሮችና ለሌሎች የፀጥታ ባለድርሻ አካላቶች ባዘጋጀው መድረክ ላይ ግዮናዊ ተልዕኮን ለታዳሚው ማስተላለፍ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ድጋፍ ለሚያሻቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)በጎንደር ከተማ በአዲስ ዓለም፣ በልደታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በገብርኤል ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያሻቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ተማሪዎቹ ከተለያዩ ት/ቤቶች እንዲሁም ከተለያዩ የትምህርት ደረጃ የተወጣጡ ሲሆን ማህበሩ በግዮን አምባሳደሮች ልዩ ጥረት ከራሱ ከማህበረሰቡ በጎ ፈቃደኛ እጅ የሰበሰበውን ደብተርና እስክርቢቶ በተጠና መልኩ ለታዳጊዎቹ አከፋፍሏል። መስከረም 15/2012 ዓ.ም

Read More