Category: አማርኛ ዜና

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጎንደርና አካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት የሚጠይቁ አካባቢዎችን በመለየት የሰላም ግንባታ በድባ ደፈጫ ቀበሌ አካሄደ

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጎንደርና አካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት የሚጠይቁ አካባቢዎችን በመለየት የሰላም ግንባታ ስራውን የቀጠለ ሲሆን በድባ ደፈጫ ቀበሌ የነበሩ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ቀደመ ኑባሬያቸው እንዲመለሱ እና እንዲጠናክሩ ያለመ ዝግጅት አድርጓል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ዙሪያ ግጭት ተፈጥሮባቸው ከነበሩ ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ድባ ደፈጫ ቀበሌ የአካባቢውን […]

Read More

በጎንደርና አካባቢው የህዝባችንን አብሮነትና ወንድማማችነት የሚያጠናክሩ ተግባራት ቀጥለዋል

በቆላድባ ከተማ እና በአይከል ከተማ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሂዷል። በቆላድባ ከተማ አዘጋጅነት የሚካሄደውን የወዳችነት የእግር ኳስ ጨዋታ ለማካሄድ የአይከል ከተማ የእግር ኳስ ቡድንን የቆላድባ ከተማ መህበረሰብ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል። እነዚህን እና መሰል ተግባራትን ልንደግፍ ይገባል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ከአይከል ወጣት የማህበሩ አባላት ጋር በዘላቂ ሰላም ዙሪያ በአይከል ከተማ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) “ወጣቶች በዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና” በሚል መሪ ቃል  የተዘጋጀ የምክከክር መድረክ በአይከል ከተማ የወጣት የማህበሩ አባላት ጋር ተካሂዷል። ከወጣቶቹ ጋር በነበረው ቆይታ የሰላም ዕሴት አስተምህሮና የተጀመረውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ተግባር መደገፍ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ጥልቅ ምክክር ማድረግ ተችሏል። ግዮን ወጣቶች ላይ በተለየ ስልት አዕምሯ ላይ እያደረገ ያለውን ዘመን […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ከአባ እንጦኒዮስ ቀበሌ ነዎሪዎች ጋር ማህበራዊ ግንኙነቶች በማጠንከር ዙሪያ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአባእንጦኒዮስ ቀበሌ ማህበራዊ ግንኙቶችን በማጠንከር ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም የዞብል ክፍለ ከተማ የፀጥታ አካላት እና የሰላም አማካሪ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል። በውይይቱም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የላሉ ማኀበራዊ ግንኙነቶች ወደቀደመ ኑባሬያቸው ለመመለሰ፤ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያችው ለመመለስ እና በግለሰብ ደረጃ ችግር ያለባቸውን ወገኖችን ለማቀራረብ ከህብረተሰቡ ኮሜቴዎች ተመርጠው ለማቀራረብ […]

Read More

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጓላወንዝ ማርያም በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር እና ማህበራዊ ግንኙነቶች በሚጠናከሩበት እና ዘላቂ ሰላምን በማስቀጠል ዙሪያ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጓላወንዝ ማርያም ማህበራዊ ግንኙቶችን በማጠንከር ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የላሉ ማኀበራዊ ግንኙነቶች ወደቀደመ ኑባሬያቸው ለመመለስ መግባባት የተደረሰ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀጣይ ከአዋሳኝ ቀበሌዎች ማህበረሰብ ጋር የጋራ መድረክ በመፍጠር የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም

Read More

የጠገዴ ስምንቱ ማይቤት ባህላዊ የፍትህ ስርዓት-ሌላዉ ወርቃማ ዕሴታችን

አፈ-ታረኩ እንደሚነግረን ከአንድ ሺህ ዓመት ዓለም ገደማ ከየመን ወደ ሀገር ቤት እንደገቡ የሚነገሩት ነገደ ዮቅጣን መሪያቸው ንጉስ ኢትዮጲስ ይባላል። ታዲያ ይህ ንጉስ ኢትዮጵያን አቅንቶ በስሙም አደላድሎ 55 ዓመታትን እንዳስተዳደረና አምስት ልጆችንም እንደወለደ የታሪክ መረጃዎች ይነግሩናል። ርስት ጉልት ያከፋፈላቸው አምስት ልጆቹም ሳባ ኖባ፣ በለው፣ ከለው፣ ላክንዱና ኖክ ይሰኛሉ። በመጀመሪያ ጠገዴን ለበለው አርማጭሆን ለከለው ርስት ሰጠ። ጠገዴን […]

Read More

በፋሲል ክ/ከተማ ሳይና ሳቢያ ቀበሌ ሸምበቂት በተሰኘች ትንሽየ ከተማ የሙስሊም ክርስቲያኑን የአብሮነት ታሪካዊ ኑባሬ የሚያስቀጥል ምክክር መድረክ ተዘጋጀ

የመድረኩ በዙሪያ አጥቢያው የሚገኙ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች፣ ከቀበሌውና ከአጎራባች ድባ ደፈጫ ግብዣ የተደረገላቸው የቀበሌ አመራሮች፣ የግዮን ሰላምና ልማት ማኅበር ሸምጋይ አባቶችና ወጣት አስተባባሪዎች፣ የአካባቢው የሁለቱ እምነት ተከታይ ነዋሪዎች ታድመዋል። የቀበሌው አስተዳዳሪ ጉባዔን መክፈቻ ሲያበስሩ መስጊዱ እንዲገነባ የአካባቢው ክርስቲያኖች ጉልህ ተዋፅዖን አስታውሰው ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የቀበሌው ሊቀመንበርና የመስጊዱ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሴ […]

Read More

በጭልጋ ወረዳ አለምፀሀይ ቀበሌ ጅባንሰግና አኩባይ ጎጦች ላይ ተፈናቅለው በአንከር አደዛ ቀበሌ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን ለመመለስ የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጭልጋ ወረዳ አለምፀሀይ ቀበሌ አስተዳደር ጅባንሰግና አኩባይ ጎጦች ላይ ተፈናቅለው በአንከር አደዛ ቀበሌ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን ከቀበሌው ማኅበረሰብ ጋር ተገናኝተው ወደነበሩበት ቀየ ለመመለስ የሚያስችል ምክክር ማካሄድ የቻለ ሲሆን በመድረኩም የማኅበሩ አባላት፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የተገኙ ተገኝተዋል። በውይይቱም የተፈናቀሉት ወገኖችን ለመመለስ የመጠለያ ጉዳይ እንዲመቻች፤ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች በዚሁ መንገድ ተጠናከረው […]

Read More

አብሮነትና መቻቻልን ማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ በጎንደሮች ጊዮርጊስ ተካሄደ

ግዮን ሰላምና ልማት ማኅበር ከዞብል ክ/ከተማ ጋር በመቀናጀት ጎንደሮች ጊዮርጊስ አካባቢ ተከታታይ የምክክር መድረኮችን አካሂዷል። ትላንት ግንቦት 28/2014 ዓ.ም የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይቱም ሰላምን በዘላቂነት የሚያሰፍን እንደነበርና የመግባቢያ ነጥቦችን በማስቀመጥ ምክክሩን ማጠናቀቅ ተችሏል። የተፈናቀሉ ወገኖች ወደነበሩበት ሕይዎት እንዲመለሱ፣ ያልታረሱ መሬቶች ካሉ በፍጥነት እንዲታረሱ፣ የላሉ ማኅበራዊ ግንኙነቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱ፣ ቂም በቀል የያዙ ተናጥላዊ ጉዳዮች በግዮን ሽማግሌዎች በዕርቅና […]

Read More

የአርማጭሆ አምስት(የደም በቃ ዛፍ ስር ፍትህ)!

በረዥም ዘመን ታሪክ እንዲሁም በገቢር ተፈትነው ከዳበሩ ስር የሰደደ ስርፀት ካላቸው ጎንደር አካባቢ ከሚከወኑ የሽምግልና ስነ-ስርዓትና ተግብሮት መሀል የአርማጭሆው “በአምስት” አንዱ ነው። *** ቃላዊ አስረጅዎች እንደሚያስረዱን አርማጭሆን ቀድመው ካቀኑ ነገስታት ቀዳሚው አፄ ናኦድ ናቸው። እኒሁ ንጉስ ታዲያ ከቀናት በአንዱ ከባድ የጥል ቋጠሮ ወደ ሸንጓቸው ሲቀርብ እንዲህ አሉ የሚል ትዕውፊታዊ የቃል ነገራ አለ። “እባካችሁ እነዚህን ጥለኞች […]

Read More