በአንድ ወቅት የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የወንድም ልጅና የእቴጌ ዘውዲቱ ባለቤት የነበሩት ራስ ጉግሳ ወሌ ደብረ ታቦር ላይ ሸንጎ ቆይተው ሲነሱ አንድ ዛፍ ስር አንዳች ክስተትን አስተዋሉ። እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ ነው ግራሩ ስር የተቀመጡት? ሲሉ አብረው ያሉትን አሽከሮቻቸውን ጠየቁ። እነርሱም እነዚህማ የተቀደደን ቤት እየሰፉ ፥ የተጣሉትን እያስተረቁ ደምን እያደረቁ ነው አሏቸው። ይህንን በጎ ግብር ሲፈፅሙ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በወገራ በተለያየ መንገድ ግጭት ውስጥ የነበሩ ከ150 በላይ ግለሰቦችን ያካተተ የእርቀ ሰላም ፕሮግራም አካሄደ
በአምባጊዮርጊስ ከተማ በደብረ ጸሐይ መድሐኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተገኙት የግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) አመራሮች በመሩት የእርቀ ሰላም ጥሪ መሰረት 150 ግለሰቦች በተለያየ መንገድ ቅር የተሰኙኙ ሰዎችን በራሳቸው ፈቃድ ተነስተው ይቅር ማባባል ችለዋል።ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ህዳር 14/3/2012 ዓ/ም
Read Moreየግዮን ወገራ ቡደን ወደ ወይላሆ ደብረ ማርያም በማቅናት ህዝቡን በማሰባሰብና በማስተማር በ30 ሰዎች መካከል የነበረውን ጥልና ግጭት በዕርቅ አስወግደዋል። ልዑክ በድኑ ግዮናዊ ትምህርት በመስጠትም ቀበሌውን የሚወክሉ ግዮናዊ አባቶችን አቋቁመዋል። ግዮን ዘወገራ ተባረኩልን!! ጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)
Read Moreማህበራችን በሁለት ወረዳዎች ማለትም በወገራና ምዕራብ ደምቢያ ተግባራትን ፈፀመ። ከጎንደር ወደ ወገራ አምባጊዮርጊስ ያቀናው ግዮናዊ ልዑክ ከግዮን አባቶችና አመቻች ወጣቶች ጋር ተወያይቶ ከዚያም ከወገራ ወረዳ ሶስት የመንግስት አመራሮች ጋር ምክክር አደርጎ ተመልሷል። በምዕራብ በለሳ እዚያው አርባያ በሚገኙ ግዮናዊያን ስራ አስፈፃሚዎች የወረዳው አስተዳደር ለቀበሌ አመራሮችና ለሌሎች የፀጥታ ባለድርሻ አካላቶች ባዘጋጀው መድረክ ላይ ግዮናዊ ተልዕኮን ለታዳሚው ማስተላለፍ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)በጎንደር ከተማ በአዲስ ዓለም፣ በልደታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በገብርኤል ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያሻቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ተማሪዎቹ ከተለያዩ ት/ቤቶች እንዲሁም ከተለያዩ የትምህርት ደረጃ የተወጣጡ ሲሆን ማህበሩ በግዮን አምባሳደሮች ልዩ ጥረት ከራሱ ከማህበረሰቡ በጎ ፈቃደኛ እጅ የሰበሰበውን ደብተርና እስክርቢቶ በተጠና መልኩ ለታዳጊዎቹ አከፋፍሏል። መስከረም 15/2012 ዓ.ም
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በርስ በርስ ግድያ አቅሉን እንዲያጣ ጣሊያን ተብትቦት የሄደውን የጥቁር ደም ጥቁር ገመድ ለመበጣጠስ አቅሙ በፈቀደው ልክ ደፋ ቀና እያለ የሚገኝ ተቋም ነው። ማህበሩ በሰሞናት የሰላም አምባሳደሮቹን ፈጥሯል። ታዳጊዎቹ ከተለያዩ ከተማችን ከሚገኙ አማተር የጥበብ ደጆች የተወጣጡ ሲሆን በትላንትናው ዕለት በጎንደር ሀይሌ ሪዞርት የሰላም አምባሳደርነት ስልጠና ማለትም የዕርቀ ሰላምን የማይተመን ዋጋ […]
Read Moreልዑኩ በዚሁ ወረዳ በሰንደባ ቀበሌ የፀጥታ ጉዳይ በነበረው ልዩ መድረክ ተገኝቶ ስለ ጥቁር ደም አስከፊነት እንዲሁም ለቅሶ ላይ ስለሚተኮስ ጥይት ሰፊ ግዮናዊ ግንዛቤ አስጨብጠዋል። የደምቢያ ማሩ ቀመስ ቆይታችን የግዮን ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት ከግዮን የወረዳው አባቶችና አመቻች ወጣቶች ጋር የጋራ ውይይት አድርጎ የወረዳው ፀጥታ አስተዳደር ባዘጋጀው መድረክ ላይም ተጋብዞ ግዮናዊ መልዕክት አስተላልፏል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት […]
Read Moreመጋቢት 12 በወገራ አምባጊዮርጊስ ከተማ ቀበሌ 02 እንዲሁም ወደ ገጠሩ ወጣ ብሎ ከምትገኘው ከምቢ ቀበሌ ልዩ ስሟ ተጎራ በሚባል መንደር የግዮን አባላት ተገኝተው ሶስት የተለያዩ የእርቅ ተግባሮችን ፈፅመዋል።“ደም በደም አይደርቅም”
Read Moreግዮን ዛሬ መጋቢት 8 በወገራ የእርቅ ገበታ ላይ ታድሞ ውሏል። በዛሬው የወረዳው ስምሪታችን በአምባጊዮርጊስ ከተማ በሚካኤል ቤተክርስቲያን የግዮን ሸምጋይ አባትና የደብሩ አስተዳዳሪ የሆኑት ቀሲስ ፈንታሁን ስለ ግዮን ፅኑ ዓላማና ስለ እርቅ ሳምንቱ አዋጅ ደብሩ ላይ ለተገኙ ምዕመናን ወምዕመናት ትልቅ እውቅናና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሰርተዋል። በጥልና ክርክር ምክንያትነት ከሶስትነት ወደ ስድስትነት የተበተነው የወይበይ ልደታ ደብር የሰንበቴ […]
Read Moreበታች አርማጭሆ ወረዳ ሦሥት ቀበሌዎች ከህግ የራቁና በተለያየ ምክንያት የተጋጩ ግለሠቦችን ለማሥታረቅና ለማሥማማት አሥታራቂ ሽማግሌዎች ተቋቁመው የአካባቢው ህብረተሠብ ያጣውን ሠላም ወደነበረበት ለመመለሥ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ሽማግሌዎች የተቋቋሙት ከሀይማኖት አባቶች ፤ከአገር ሽማግሎች፤ከሤቶች እና ከወጣቶች ነው። ማንኛውም የአርማጭሆን ሠላም ፈላጊ በአካባቢው ም ያለ ከአካባቢው ውጭ የሆነ እና ከአገር ውጭ ያለም ቢሆን ከላይ የተዘረዘሩትን አሥታራቂ ሽማግሌዎች በፀሎት፤በሐሣብ እና […]
Read More