ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምከንያት የላሉ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ፣በአካባቢው የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት፣ማህበራዊ ተቋማትን ስራ ለማስጀመር እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ የእርቅ መርሀ-ግብር አካሄደ። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር በቅማንት እና አማራ […]
Read Moreጎንደር ከተማ በሀገራችን ታሪክ 200 ዓመታትን በማዕከልነት ቆማ የአፍሪቃ ቀንድ የስልጣኔ መናገሻ ነበረች፡፡ ጎንደር የስጋና የነፍስ ውህድ በመሆን ሰላምና ፍቅር ከምትሰብክባቸው አጸዶቿ መሀል የጃንተከል ሽምግልና እንዲሁም የዕርቅ ቀየዋ ዕርቅ ቤት ይገኝበታል፡፡ የጃንተከል ባህላዊ ፍትህ “ጃን ማለት ንጉስ ነው ተከል ደግሞ መትከል የቀለሱት ጎጆ ሁለቱ ተጋብተው ይሆናል የጸና ንጉስ የተከለው (ፍሬዘር እንግዳ፣ 2010) አጤ ፋሲል ወደ […]
Read Moreግዮን ሰላምና ልማት ማኅበር በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ቀበሌ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ከአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው በመመለስ ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ፤ በአካባቢው የቅማንት እና አማራ ወገኖች መካከል የነበረው አብሮነት ወደ ድሮው ግንኙነት ስለሚመለስበት እና በአጠቃላይ በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ስለሚሰፍንበት መንገድ ጥልቅ ውይይት አድርጓል። በውይይቱም የላይ አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ማለደ፤ የወረዳው የአስተዳደር ፀጥታ ኃላፊ አቶ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ከተማ ፋሲል ክ/ከተማ ስር የሚገኙ ሳይሳ ሳቢያና ድባ ደፈጫ፤ በላይ አርማጭሆ የባንብሎ ጭጋሳ ቀበሌ፤ በጎንደር ዙሪያ ስሆር ጉልቶች ቀበሌ የወረዳና ቀበሌ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት፣ የሕዝብ እንደራሴዎች በንቃት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በምክክሩም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች ተጠናከረው እንዲቀጥሉ የሚያስችሉ ተከታታይ የማሕበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን በቀጣይነት ለማካሄድ፤በሁሉም ቀበሌዎች በራ ጠፋ የሚሉ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም በድባ አቦ መንደር በመገኘት ፍሬያማ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይቱም ተሳታፊዎች በአካባቢው ተፈጥሮ ከነበረው ችግር በኃላ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም
Read Moreማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጎንደርና አካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት የሚጠይቁ አካባቢዎችን በመለየት የሰላም ግንባታ ስራውን የቀጠለ ሲሆን በድባ ደፈጫ ቀበሌ የነበሩ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ቀደመ ኑባሬያቸው እንዲመለሱ እና እንዲጠናክሩ ያለመ ዝግጅት አድርጓል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ዙሪያ ግጭት ተፈጥሮባቸው ከነበሩ ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ድባ ደፈጫ ቀበሌ የአካባቢውን […]
Read Moreበቆላድባ ከተማ እና በአይከል ከተማ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሂዷል። በቆላድባ ከተማ አዘጋጅነት የሚካሄደውን የወዳችነት የእግር ኳስ ጨዋታ ለማካሄድ የአይከል ከተማ የእግር ኳስ ቡድንን የቆላድባ ከተማ መህበረሰብ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል። እነዚህን እና መሰል ተግባራትን ልንደግፍ ይገባል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) “ወጣቶች በዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የምክከክር መድረክ በአይከል ከተማ የወጣት የማህበሩ አባላት ጋር ተካሂዷል። ከወጣቶቹ ጋር በነበረው ቆይታ የሰላም ዕሴት አስተምህሮና የተጀመረውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ተግባር መደገፍ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ጥልቅ ምክክር ማድረግ ተችሏል። ግዮን ወጣቶች ላይ በተለየ ስልት አዕምሯ ላይ እያደረገ ያለውን ዘመን […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአባእንጦኒዮስ ቀበሌ ማህበራዊ ግንኙቶችን በማጠንከር ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም የዞብል ክፍለ ከተማ የፀጥታ አካላት እና የሰላም አማካሪ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል። በውይይቱም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የላሉ ማኀበራዊ ግንኙነቶች ወደቀደመ ኑባሬያቸው ለመመለሰ፤ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያችው ለመመለስ እና በግለሰብ ደረጃ ችግር ያለባቸውን ወገኖችን ለማቀራረብ ከህብረተሰቡ ኮሜቴዎች ተመርጠው ለማቀራረብ […]
Read Moreግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጓላወንዝ ማርያም ማህበራዊ ግንኙቶችን በማጠንከር ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የላሉ ማኀበራዊ ግንኙነቶች ወደቀደመ ኑባሬያቸው ለመመለስ መግባባት የተደረሰ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀጣይ ከአዋሳኝ ቀበሌዎች ማህበረሰብ ጋር የጋራ መድረክ በመፍጠር የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል። ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም
Read More