ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአባእንጦኒዮስ ቀበሌ ማህበራዊ ግንኙቶችን በማጠንከር ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም የዞብል ክፍለ ከተማ የፀጥታ አካላት እና የሰላም አማካሪ ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል። በውይይቱም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የላሉ ማኀበራዊ ግንኙነቶች ወደቀደመ ኑባሬያቸው ለመመለሰ፤ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያችው ለመመለስ እና በግለሰብ ደረጃ ችግር ያለባቸውን ወገኖችን ለማቀራረብ ከህብረተሰቡ ኮሜቴዎች ተመርጠው ለማቀራረብ ወደ ተግባር የሚያስገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)
ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም



