ማኅበራችን መንገዘዝ ከተሰኘ የኪነጥበብ ድርጅት ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ 

አዲስ አበባ የሚገኘው መገዘዝ የኪነጥበብ ድርጅት በታዋቂው አርቲስት አንዱዓለም አባተ (የአፀደ ልጅ) የተመሰረተና የሚመራ ሲሆን በሰላም ዕሴት ግንባታና ግጭት መከላከል ላይ ያተኮረ ስራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች መክረናል። በኪነጥበብ መሣሪያነት የግጭት ቅድመ መከላከል ተግባራትን በተቀናጀ መንገድ ለመስራት የጋራ መግባቢያ ሰነድ (Memorandum of Understanding) ተፈራርመናል።

ሰላማችሁ የበዛ ይሁን

ግዮን ሰላምና ልማት ማህበር

ታህሳስ፣ 2014 ዓ.ም