ማኅበራችን ከዩስኤድ ጋር በመስራት የሚታወቀው ዲኤክሲስ ኮንሰልቲንግ ግሩፕ ግምታቸው ከ180,000 ብር በላይ የሚሆኑ የቢሮ ግብዓቶችን ለማኅበራችን አበርክቷል። ግብዓቶቹም ደረጃቸውን የጠበቁ ላፕቶፖች፣ ኮምፒዩተሮች፣ ፕሪንተርና ሌሎች ናቸው። የተበረከቱት ግብዓቶች ባለፉት ወራት በድርጅታቸው ኦቲአይ አጋርነት በሰራነው “ወጣቶችን ከሀይማኖት አባቶች ጋር የማገናኘት የውይይት ማዕቀፍ” በብቁ አተገባበራችን እንደሆነ በመጥቀስ ከበርካታ አጋር ሲቪክ ማኅበራት ጋር በንፃሬ የተሻለ የስራ አፈፃፀም በማስመዝገባችን እንደተበረከተልን በኤስኤድ ኦቲአይ የኢትዮጲያ ድጋፍ ፕሮግራም የአማራ ክልል ፕሮግራም ማናጀር አቶ ተመስገን ዓለሙ ተናግረዋል። በተለይም በአማራ ክልል የድርጅቱ ፕሮግራም ዲቨሎፕመንት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አንተነህ ተስፋሁን ከማኅበራችን ጋር ቀጣይ ተግባራትን አብሮ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ማኅበራችን ላይ ልዩ እምነት እንዳሳደሩ አሳስበዋል። ማኅበራችንም ስለተደረገለት ሽልማትና ስለተጣለበት እምነት ለድርጅቱ ምስጋና አቅርቧል።
ሰላማችሁ የበዛ ይሁን
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) የካቲት፣ 2014 ዓ.ም

