ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በሁለት የጎንደር የገጠር ቀበሌዎች በመገኘት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኙ አጀንዳዎች ዙሪያ ማኀበረሰብ አቀፍ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) አስተባባሪነት ግንቦት 14/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች በአባ እንጢንዎስና በብላጅግ ድባርቃ ቀበሌ በመገኘት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኙ አጀንዳዎች ዙሪያ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት በጥልቅ ተመክሯል። የምክክሩ ዓብይ ጉዳይም ከአሁን በፊት በአማራና ቅማንት ወንድማማች ማኅበረሰቦች መካከል እኩያን ቀስቅሰውት በነበረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ እንግልት የተዳረጉ ወገኖችን በማቀራረብ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በሚያስገኝ ጉዳይ የማኅበረሰብን፣ የመንግስት ሚናን የለየ የቀጣይ ተግባራት በሚገባ ለይቶ ያስቀመጠ ሕዝባዊ መድረክ ነበር።

“ሰላማችሁ የበዛ ይሁን”

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)

ግንቦት፣ 2014 ዓ.ም