ግዮን ሰላምና ልማት ማኅበር ከዞብል ክ/ከተማ ጋር በመቀናጀት ጎንደሮች ጊዮርጊስ አካባቢ ተከታታይ የምክክር መድረኮችን አካሂዷል። ትላንት ግንቦት 28/2014 ዓ.ም የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይቱም ሰላምን በዘላቂነት የሚያሰፍን እንደነበርና የመግባቢያ ነጥቦችን በማስቀመጥ ምክክሩን ማጠናቀቅ ተችሏል። የተፈናቀሉ ወገኖች ወደነበሩበት ሕይዎት እንዲመለሱ፣ ያልታረሱ መሬቶች ካሉ በፍጥነት እንዲታረሱ፣ የላሉ ማኅበራዊ ግንኙነቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱ፣ ቂም በቀል የያዙ ተናጥላዊ ጉዳዮች በግዮን ሽማግሌዎች በዕርቅና ሽምግልና እንዲዳኙ በማለት ሁለቱ ወንድማማች ማኅበረሰቦችን መሀል ታላቅ ተግባቦት መፍጠር ተችሏል።
ግዮን ሰላምና ልማት ማህበር (ግሰልማ)
ግንቦት 28/2014 ዓ.ም

