ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በሁለት ወረዳዎች ከሚገኙ የመንግስት አመራሮች ጋር በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ምክክር አደረገ

ማህበራችን በሁለት ወረዳዎች ማለትም በወገራና ምዕራብ ደምቢያ ተግባራትን ፈፀመ። ከጎንደር ወደ ወገራ አምባጊዮርጊስ ያቀናው ግዮናዊ ልዑክ ከግዮን አባቶችና አመቻች ወጣቶች ጋር ተወያይቶ ከዚያም ከወገራ ወረዳ ሶስት የመንግስት አመራሮች ጋር ምክክር አደርጎ ተመልሷል። በምዕራብ በለሳ እዚያው አርባያ በሚገኙ ግዮናዊያን ስራ አስፈፃሚዎች የወረዳው አስተዳደር ለቀበሌ አመራሮችና ለሌሎች የፀጥታ ባለድርሻ አካላቶች ባዘጋጀው መድረክ ላይ ግዮናዊ ተልዕኮን ለታዳሚው ማስተላለፍ ችለዋል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)