ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት በሚል የውይይት መድረክ አዘጋጀ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር “በአይከል ከተማ እና በጎንደር ከተማ ዙሪያ ቀበሌዎች ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት በሚል የውይይት መድረክ” ለማዘጋጀት ከአመቻች ወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ሸምጋይ አባቶች ጋር ጥቅምት 12 እና 13 2014 ዓ/ም የምክክር መድረክ በጎንደር ከተማ ኤጂ ሆቴል ማካሄድ ችሏል። ከጎንደር ከተማና አይከል ከተማ የተወጣጡ አመቻች ወጣቶች፣ የሀይማኖት መሪዎችና ሸምጋይ አባቶች የወጣቶችን ውይይት ለማካሄድ የተዘጋጀውን አጀንዳ አቅርቦ ማስተቸት የተቻለ ሲሆን ከተወያዮቹ የተለያዩ ምክረ ሀሳቦችንም ማግኘት ተችሏል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር

ጥቅምት 14/2014 ዓ/ም

ጎንደር፤ኢትዮጲያ