ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) “ወጣቶች በዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የምክከክር መድረክ በአይከል ከተማ የወጣት የማህበሩ አባላት ጋር ተካሂዷል። ከወጣቶቹ ጋር በነበረው ቆይታ የሰላም ዕሴት አስተምህሮና የተጀመረውን የዘላቂ ሰላም ግንባታ ተግባር መደገፍ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ጥልቅ ምክክር ማድረግ ተችሏል። ግዮን ወጣቶች ላይ በተለየ ስልት አዕምሯ ላይ እያደረገ ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ገቢር በማድነቅ ከማኅበሩ ጎን ቆመው ለዘላቂ ሰላም እንደሚሰሩ በይፋ ሀሳባቸውን አቅርበዋል። በፍፃሜም ማኅበሩ በአይከል ከተማ የወጣቶች አደረጃጀት የሚጠናከርበትን ስልት በመቀየስ ጉባዔው ተጠናቋል።
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)
ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም







