ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጓላወንዝ ማርያም በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር እና ማህበራዊ ግንኙነቶች በሚጠናከሩበት እና ዘላቂ ሰላምን በማስቀጠል ዙሪያ ውይይት አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጓላወንዝ ማርያም ማህበራዊ ግንኙቶችን በማጠንከር ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱም በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የላሉ ማኀበራዊ ግንኙነቶች ወደቀደመ ኑባሬያቸው ለመመለስ መግባባት የተደረሰ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም በቀጣይ ከአዋሳኝ ቀበሌዎች ማህበረሰብ ጋር የጋራ መድረክ በመፍጠር የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)

ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም