ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ የእርቅ መርሀ-ግብር አካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምከንያት የላሉ ማህበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ፣በአካባቢው የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት፣ማህበራዊ ተቋማትን ስራ ለማስጀመር እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ የእርቅ መርሀ-ግብር አካሄደ።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደሮች ማርያም/ብላጅግ ዳብርቃ ቀበሌ በመገኘት በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር በቅማንት እና አማራ ወገኖች መካከል የነበረው አብሮነት ወደ ድሮው ግንኙነት ለመመለስ እና በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ የእርቅ መርሀ-ግብር አካሄዷል። በፕሮግራሙም የላይ አርማጭሆ ወረዳ የአስተዳደር ፀጥታ ኃላፊ አቶ ማንዴ ወ/ማሪያም፤ የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዮት፣ የወረዳው የፀጥታ አካላት፣የግዮን ሰላምና ልማት አባላት እና ብዛት ያለው የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል። በእርቅ መርሀ-ግብሩ ከሁለቱ ቀበሌዎች የተወጣጡት የማህበረሰብ አካላት ባለፉት ዓመታት በመካከላችን በተፈጠረው ችግር ምክንያት ብዙ ጉዳት ቢደርስብንም ይቅር ተባብለን ለቀጣይ አብሮነታችን አብረን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል። ከላይ አርማጭሆ ወረዳ እና ማራኪ ክፍለ ከተማ የተገኙ አመራሮችም በአካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ቀጣይነት ያለው የቅንጅት ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የተፈናቀሉ ወገኖች በቀጣይ ቀናት በሁሉም ማህበረሰብ ርብርብ ለማቋቋም፣የማህበረሰቡን የቆየ አብሮነት ለመመለስ እና ማህበራዊ ተቋማትን ለማጠናከር በመግባባት የእርቅ መርሀ-ግብሩ ተጠናቋል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)