ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በአባ እንጦኒዮስ ቀበሌ በሚገኘው የአባ እንጦኒዮስ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በአካባቢውን ዘላቂ ሰላም ዙሪያ የሰላም አስተምህሮ አካሄደ

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) የማህበሩ አባላት፣የቀበሌው አመራሮች እና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት የአባ እንጦኒዮስ ትምህርት ቤት በመገኘት የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ስለሚጠቅበት እና በማህበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ተማሪዎች አውንታዊ ሚናቸውን በሚወጡበት ዙሪያ የሰላም አስተምህሮ ሰጥቷል። በዚህ ወቅትም ተማሪዎች ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለፁ ሲሆን ማህበራችን በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው ችግር የተወጣውን ሚናም አወድሰዋል። በወቅቱ የነበሩ የማህበሩ አባላትም ተማሪዎች ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራው በቀጣይነት በሌሎች ቀበሌዎችም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)