ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በርስ በርስ ግድያ አቅሉን እንዲያጣ ጣሊያን ተብትቦት የሄደውን የጥቁር ደም ጥቁር ገመድ ለመበጣጠስ አቅሙ በፈቀደው ልክ ደፋ ቀና እያለ የሚገኝ ተቋም ነው። ማህበሩ በሰሞናት የሰላም አምባሳደሮቹን ፈጥሯል። ታዳጊዎቹ ከተለያዩ ከተማችን ከሚገኙ አማተር የጥበብ ደጆች የተወጣጡ ሲሆን በትላንትናው ዕለት በጎንደር ሀይሌ ሪዞርት የሰላም አምባሳደርነት ስልጠና ማለትም የዕርቀ ሰላምን የማይተመን ዋጋ አሳይቶ እንዲያሳዩ በተገኘው አጋጣሚ አደራ ነገረ ሰላምን ስበኩ አደራ ነገረ ፍቅርን አስተምሩ በማለት የግዮን የባለቤትነት ማዕረግ ሰጥቷቸዋል። እናንተም እነኝህ በጎ የሰላም አምባሳደሮቻችን ደጃችሁ ሲቆሙ ጆሮ አትንፈጓቸው…? ለጠየቁት ሁሉ በጎ ምላሽ አድሏቸው!!!
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)




