ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)በጎንደር ከተማ በአዲስ ዓለም፣ በልደታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በገብርኤል ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያሻቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ተማሪዎቹ ከተለያዩ ት/ቤቶች እንዲሁም ከተለያዩ የትምህርት ደረጃ የተወጣጡ ሲሆን ማህበሩ በግዮን አምባሳደሮች ልዩ ጥረት ከራሱ ከማህበረሰቡ በጎ ፈቃደኛ እጅ የሰበሰበውን ደብተርና እስክርቢቶ በተጠና መልኩ ለታዳጊዎቹ አከፋፍሏል።
መስከረም 15/2012 ዓ.ም

