ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር የገጠር ቀበሌዎች በመገኘት የእርቅ፣ሰላም፣መቻቻል መልዕክቶችን የማድረስ እና የእርቅ ተግባራትን ማከናወኑን ቀጥሏል

ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ገጠር ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ በግዮናዊ ሸምጋይ አባቶች አማካኝነት መልዕክተ እርቅን፣ሰላምን፣መቻቻልን እና መልዕክተ ግዮንን አድርሰዋል። አምላክ በወደደው እና በፈቀደው መሠረትም በግዮን አባቶች አማካኝነት አለመግባባቶች ይቅር በማባባል ሰላም እንዲወርድ ተደርጓል። የህዝብ ለህዝብ ተግባቦት እንዲመጣ የአባቶቹን አሰረ ፍኖት ተከትሎ ለመጓዝ ወገኑንና ሞራሉን ያቀናጀው ማህበራችን በተቀዳሚ አጀንዳው የህዝብ ለህዝብ አንድነት እንዲመጣ አንግቦ ከተነሳ ጀምሮ ብዙ ተግባራትን እናከናወነ ነው።

መጋቢት 2015 ዓ.ም

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)