ግዮን የእርቀ ሰላምና ልማት ማህበር “የእርቅ ሳምንት”:- የሁለት ወራት የእርቅ ተግባር  በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ  አስጀመረ

ግዮን የእርቀ ሰላምና ልማት ማህበር “የእርቅ ሳምንት” በሚል የሁለት ወራት መርሃግብር በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሳንጃ ከተማ አስጀመረ። ይህ ፕሮግራም በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት የሚደረግ ሲሆን በአካባቢው ካለው የችግሩ ስፋት አኳያ በተመረጡ አካባቢዎች ለተከታታይ 2 ወራት የሚከናወን ነው። በመርሃ ግብሩ የሚከናወነውን የእርቅ ተግባር በተመለከተ፥ ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ•ም በጎ ፈቃደኞች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሳንጃ ከተማ ከሚገኙ የድል ፋና ት/ቤት መምህራንና ተማሪዎች ጋር በምስሉ በሚታየው ሁኔታ ምክክር ሲያደርጉ ውለዋል።

ደም በደም አይደርቅም!