ግዮን ዛሬ መጋቢት 8 በወገራ የእርቅ ገበታ ላይ ታድሞ ውሏል። በዛሬው የወረዳው ስምሪታችን በአምባጊዮርጊስ ከተማ በሚካኤል ቤተክርስቲያን የግዮን ሸምጋይ አባትና የደብሩ አስተዳዳሪ የሆኑት ቀሲስ ፈንታሁን ስለ ግዮን ፅኑ ዓላማና ስለ እርቅ ሳምንቱ አዋጅ ደብሩ ላይ ለተገኙ ምዕመናን ወምዕመናት ትልቅ እውቅናና የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ሰርተዋል። በጥልና ክርክር ምክንያትነት ከሶስትነት ወደ ስድስትነት የተበተነው የወይበይ ልደታ ደብር የሰንበቴ ፅዋ ወደ ነበረው የሶስትነት ኖርማላይዜሽን ለማምጣት በየሰንበቴው በመገኘት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በይደር ለማየት ለመጋቢት 22 ቀጠሮ መያዝ የተቻለበት መልካም አጋጣሚ ነበረ።
“ደም በደም አይደርቅም”

