በታች አርማጭሆ ወረዳ ሦሥት ቀበሌዎች ከህግ የራቁና በተለያየ ምክንያት የተጋጩ ግለሠቦችን ለማሥታረቅና ለማሥማማት አሥታራቂ ሽማግሌዎች ተቋቁመው የአካባቢው ህብረተሠብ ያጣውን ሠላም ወደነበረበት ለመመለሥ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ሽማግሌዎች የተቋቋሙት ከሀይማኖት አባቶች ፤ከአገር ሽማግሎች፤ከሤቶች እና ከወጣቶች ነው።
ማንኛውም የአርማጭሆን ሠላም ፈላጊ በአካባቢው ም ያለ ከአካባቢው ውጭ የሆነ እና ከአገር ውጭ ያለም ቢሆን ከላይ የተዘረዘሩትን አሥታራቂ ሽማግሌዎች በፀሎት፤በሐሣብ እና የተለያዩ ኢንፎርሜሸን በመሥጠት በምክር ትረዱን ዘንድ እየጠየቅን ከህግ የራቁም የበደሉትን ክሠው የወሠዱትን መልሠው ከላይ በተዘረዘሩት አማካኝነት ወደወገናቸው እንዲቀላቀሉ እናድርግ።

