ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ከተማ ፋሲል ክ/ከተማ ስር የሚገኙ ሳይሳ ሳቢያና ድባ ደፈጫ፤ በላይ አርማጭሆ የባንብሎ ጭጋሳ ቀበሌ፤ በጎንደር ዙሪያ ስሆር ጉልቶች ቀበሌ የወረዳና ቀበሌ አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት፣ የሕዝብ እንደራሴዎች በንቃት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በምክክሩም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች ተጠናከረው እንዲቀጥሉ የሚያስችሉ ተከታታይ የማሕበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን በቀጣይነት ለማካሄድ፤በሁሉም ቀበሌዎች በራ ጠፋ የሚሉ የሌቦችን ዝርፊያ በጋራ ለመታገልና ለህግ አጋልጦ ለመስጠት፤የስጋት አየር ከቧት ከወገራ ወረዳ እስከ ጎንደር ከተማ ዘልቃ የምትገባው የኩዳድ መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ነፃ ወለል እንድትሆንና የሁሉም ቀበሌ የፀጥታ አካላት በቅንጅት ክትትልና ጥበቃ ለማድረግ የጋራ ተግባቦት ላይ ተደርሷል።
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)




