የሙርሀንገብ ዳኝነት እና በለሳ—ነባር ይትባህሉ ወደ ፊት ሊመጣ የሚገባዉ ስርዓት

በለሳ እና አካባቢዉን ከእርስ በርስ መዳማት ጋር በተያያዘ ያለውን ስም ለመፋቅና አካባቢዉን ከስጋት አርነት ለማውጣት ከተጉት መሀል የሙርሀንገብ ኪዳነ ምህረት ፍርድ ሸንጎዎች አንዱ ናቸው። በሙርሀንገብ ሸንጎ አያሌ የግጭት መዝገቦች ተዘግተዋል። ደም የተቃቡ በሽምግልና ቋንቋ ተግባብተው ደም አድርቀዋል። በዚህ የሙርሀንገብ ዳኝነት ወጥ የሆነና ሁሉም ማህበረሰብ ንቁ ሱታፌ ያደረገበት የማስቻያ አንቀፆች ተቀምጦላቸዋል። ለአብነት ምርሀንገቦች የጥቁርና ቀይ ደምን ሲዳኙ አልሞ አቅዶ የግፍ ግፍ የገደለ፣ ከጠዋት ከማታ ሳያስብ ሳያልም በድንገቴ ወንድሙን ግዳይ የጣለ በሚል ከፋፍለው ደንብተውለታል። በተለይ ስለ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ያለው አተያየ በውዴታ ወይንስ ያለውዴታ በግዴታ በሚል ፈርጅ ከፋፍሎ ደንብ ሰርቷል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)

ሐምሌ፣ 2014 ዓ.ም