ወገራና ባህላዊ የፍትህ መስጫው-ዶሮ ማጣፈጫ (ሌላዉ ወደፊት ሊመጣ የሚገባውና የተደበቀዉ እሴት)

የዶሮ ማጣፈጫ ባህላዊ ፍትህ በወገራ ወረዳ ኖራ ፃድቃን ልዩ ስሟ ዶሮ ማጣፈጫ በሚሏት ኮረብታማ ስፍራ ይከወን የነበርና ሙሉ ስሜን በጌምድር በፈረስ በበቅሎ ተጉዞ ለይግባኝ አቤት ይልበት የነበር የሁለቱ ጠቅላይ ግዛቶች ማዕከላዊ መገናኛ ነጥብም ነበረች። በዚህ የዶሮ ማጣፈጫ የይግባኝ ዳኝነት ጉልበት እንዲያገኝ ስመ ማህተም ከነበራቸው ሰዎች መሀል ብላታ ቦጋለ፣ ግራዝማች አለሙ፣ ፊታውራሪ ከበደ ጀምበሬ፣ ብላታ ላቀው፣ ዋለ ጌታሁን፣ ማዘንጊያ ገብሩ ይገኙበታል። ይህ ዳኝነት ደጃች አያሌው ብሩ የሰሜን ጠቅላይ ግዛት ገዥ ራስ ጉግሳ ወሌ የበጌምደር ገዥ በነበሩበት ወቅት በይበልጥ እውቅና ተሰጥቶት አግቦም ተበጅቶለት ይከወን እንደነበርም ይነገራል። ከልዩ መገለጫዉ ዉስጥ ለአብነት ያህል ወንድሙን በግፍ ለገደለ ደም ላፈሰሰ ሰው የደም ጋና (የደም ካሳው) እስከ 7 ትውልድ የሚገኝ የመክፈል ዕዳ እንዳለበት ኃላፊነት እንዲወስድ ያስገድዳል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)