የመድረኩ በዙሪያ አጥቢያው የሚገኙ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች፣ ከቀበሌውና ከአጎራባች ድባ ደፈጫ ግብዣ የተደረገላቸው የቀበሌ አመራሮች፣ የግዮን ሰላምና ልማት ማኅበር ሸምጋይ አባቶችና ወጣት አስተባባሪዎች፣ የአካባቢው የሁለቱ እምነት ተከታይ ነዋሪዎች ታድመዋል። የቀበሌው አስተዳዳሪ ጉባዔን መክፈቻ ሲያበስሩ መስጊዱ እንዲገነባ የአካባቢው ክርስቲያኖች ጉልህ ተዋፅዖን አስታውሰው ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የቀበሌው ሊቀመንበርና የመስጊዱ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሴ ዛሬ በዚህ መስጊድ ቁጭ ብለን በጋራ ለመምከር የተነሳንበት ሌላ የመወያያ አዳራሽ አጥተን አልነበረም ሲሉ አስረድተዋል። መስጊዱም የጋራ ሀብታችን የጣምራ ቤታችንን የአብሮነት ማሳያችን መሆኑን ለማዘከር ነበር ሲሉም ተናግረዋል። አብሮነታችንን ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ክፉ ኃይሎችን በመምከር በመዘከር ፈጣሪ ልቡናቸውን እንዲመልስ በመፀለይ የሰላማቸውን ጠብቆት ለማረጋገጥ፤ የተጀመረውን መስጊዳችንን ደግሞ ለፍፃሜ ለማብቃት ሁሉም ክርስቲያን ሙስሊሙ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት በሚል ውይይቱ ሐምሌ 04/2014 ዓ.ም ተጠናቋል።





