በጭልጋ ወረዳ አለምፀሀይ ቀበሌ ጅባንሰግና አኩባይ ጎጦች ላይ ተፈናቅለው በአንከር አደዛ ቀበሌ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን ለመመለስ የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጭልጋ ወረዳ አለምፀሀይ ቀበሌ አስተዳደር ጅባንሰግና አኩባይ ጎጦች ላይ ተፈናቅለው በአንከር አደዛ ቀበሌ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን ከቀበሌው ማኅበረሰብ ጋር ተገናኝተው ወደነበሩበት ቀየ ለመመለስ የሚያስችል ምክክር ማካሄድ የቻለ ሲሆን በመድረኩም የማኅበሩ አባላት፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የተገኙ ተገኝተዋል። በውይይቱም የተፈናቀሉት ወገኖችን ለመመለስ የመጠለያ ጉዳይ እንዲመቻች፤ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶች በዚሁ መንገድ ተጠናከረው እንዲቀጥሉ እና ደራሽ የሆኑ የእርዳታ እህል ድጋፎች በአፋጣኝ እንዲደርሱ ተወያዮች የጠየቁ ሲሆን ለዘላቂ ሰላም አውንታዊ ሚና ለመወጣት ያላቸውን ቁርጠኝነትም ገልፀዋል።

ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)

ሐምሌ 3፣ 2014 ዓ.ም