በእርቅ ፕሮግራሙ የጊዮን አስታራቂ ማህበር እንዲሁም የዞብል ክፍለ ከተማ በሰላም አመካሪ እና የዞብል ክፍለ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፉ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አስራደ ፣ የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት ፕሮግራሙ ተካሂዷል።
የአማራና የቅማንት ህዝባዊ አንድነቱን በማጠናከር የነበር አብሮነታችን በማሳደግ እና እንደጥንቱ የአባቶቻችን ዉበት እና ለዛ በማያዝ የነበር አብሮነታችን ለማስቀጠል የውሰጥ አንድነታች ለሀገራችን እና ለክልላችን ብሎም ለአካባቢያችን አንድነትን በማጠናከር በውሰጥ ያሉን ፅንፈኛ ሀይሎች በመታገል አብሮነታችን የማስቀጠል ኃላፊነት አለብን ተብሏል።
እግዚአብሔር የፈጠራቸዉን የሰው ልጆች አንዱ ለአንዱ የመኖር መርህን ተከትሎ መተሳሰብ እና መረዳዳት ሲገባ ተፈናቀሎ እና አፈናቅሎ ሁልጊዜ የሰውን ልጅ እርዳታ በመሰጠት እና በመረዳት ያደገ የለምና የቅማንት እና የአማራ ወንድማማችነት በማጠናከር እና በማስቀጠል መንግስትም የራሱን ድርሻ በመወጣት በየአካባቢው የህግ የበላይነት ማሰከበርና ሰራ መሠራት እንደሚገባ ተገልጿል።
በየአካባቢው ከሚሰጠን አጀንዳ ተጠልፎ ከመውደቅ ይልቅ የሁለቱን ወንድማማችነት በማጠናከር ወደቂያቸው በመመለስ ህዝቡና መንግሰት ሰፊውን ድርሻ የሚወሰድ በመሆኑ ሌባን ሌባ በማለት እና ፅንፈኝነት አምርሮ በመታገል አድብ እንዲገዛ ማድረግ የመንግስት እና የህዝብ በመሆኑ ሁላችንም ለአብሮነት እና ለአንድነታችን መታገል ይኖርብናል ተብሏል።
የሁለቱን የማህበረሰብ ክፍል እንደቀደመው ለማድረግ ችግሮችን በመነጋገር በመፍታት ቅሬታን በማስወገድ አብሮነታችንን ማስከበር እና ማጠንከር አለብን ሲሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ለሁለቱም የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሆኑ አስታራቂ ሽማግሌዎችን በመምረጥ ውይይት ተጠናቅቋል።




