ያለ መግባባት ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችለውን ባህላዊ የሽምግልና የዳኝነት ስርዓት ማጠናከር ይገባል ተባለ።
የወሎ ዩኒበርስቲ ፣ጊዎን የዕርቀ ሰላምና ልማት የበጎ አድራጎት ማህበር፣ፕሮ ዲቨሎፕመንት ኔት ወርክና ትራንዚሽን ኢኒሽቲቭ የተባለ የአሜሪካን ተራዶ ድርጅቶች በመተባበር በሰላም አብሮ የመኖር ባህል ለማሳደግ የሚያስቾል የልምድ ልውውጥና የእርስ በርዕስ የመማማር አውደ ጥናት በጎንደር ከተማ ተካሒዷል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የጊዎን ዕርቀ ሰላምና ልማት የበጎ አድራጎት ማህበር ሊቀ መንበር አቶ አራጋው ገበየ እንደገለፁት ባህላዊ የዕርቀ ሰላም ስርዓት በህብረተስቡ ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችንና ግጭቶቾን በራስ አቅም ለመፍታት ያስችላሉ።
ጊዎን የዕርቀ ስላም የበጎ አድራጎት ማህበር ግጭቶች ከመፈጠራቸው በፊት ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ ግጭቶችን የግጭት መንስኤዎችን በማጥናት ለመፍታት ቅድሚያ ይስጣል።ግጭቱ ከተፈጠረ ደግሞ ችግሩን በባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት መስረት ስፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ለመፍታት ይስራል ብለዋል።
በአካባቢያችን በርካታ ውጤታማ የሆኑ ባህላዊ የሽምግልና የዕርቅ አብፈታት ስነ-ስርዓቶች አሉን ያሉት የማህበሩ ሊቀመንበር በወሎ ዩኒበርስቲ ተጠንቶ በፕሮ ዲቨሎፕመንት ኔት ወርክና በትራንዚሽን ኢኒሽቲቭ የቀረበው የወሎ ህዝብ ባህላዊ የዕርቀ ስላም ስርዓት ተሞክሮ ከወሎ ህዝብ የተሻለውን ተሞክሮ እንድንቀስምና በአካባቢው ትኩረት ያልተስጣቸውን የዕርቅ አፈታት ስነ-ስርዓት ጎልቶ እንዲወጣ ዕድል ይስጣል ሲሉ አቶ አራጋው ገልፀዋል።
የአካባቢውን ባህላዊ የዕርቅ አፈታት ስነ-ስርዓት ለማሳደግ መንግስት ፣ሚዲያ፣ ምሁራን የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች
የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የፕሮ ዲቨሎፕመንት ኔት ወርክ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ መስፍን ተክለ አብ ደግሞ ወርክ ሾፑ የወሎን ህዝብ ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት በማስፋት በየአካባቢው የሚፈጠሩ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት እንዲቻል ታስቦ በውሎ ዩኒበርስቲ ምሁራን የተጠናና በዶክመታሪ መልክ ተዘጋጅት ለወርክ ሾፑ ተሳታፊዎች ማቅረብ መቻሉን ገልወርክ ሾፑ በተመረጡ አምስት የአማራ ክልል ከተሞች እየተካሔደ መሆኑን ገልፀዋል።
በወርክ ሾፑም በየአካባቢው ያሉ የዕርቀ ስላም ስርዓቶች ያለ ማንም ጣልቃ ገብነትና ተፅኖ ማከናወን ከተቻለ ሊፈጠሩ የሚችሉ ግጭቶችን በማስቀረትና ከተፈጠሩም ችግሩን ለመፍታት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻል የወርክ ሾፑ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል ሲሉ አስተያየታቸውን ስጥተዋል።
ከወርክ ሾፑ ተሳታፊዎች መካከል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር አስካለ ካሳሁን ደግሞ የወሎን የሀይማኖት አባቶች የዕርቀ ሰላም አፈታት አፈታት ስነ-ስርዓት ልምድ በመቅስምና በአካባቢያችን ከፍተኛ ጠቀሜታ የነበራቸውና አሁን እየተረሱና በተለያዩ ምክኒያቶች እየተዳከሙ የመጡ የዕርቀ ስላም ስርዓቶችን ማሳደግ እንደሚገባን አውቀት መገብየት መቻላቸውን ጠቁመዋል።ባገኙት ግንዛቤ መስረትም ለስላም እንደሚስሩም አስተያየታቸውን ስጥተዋል ።
ሌላው የወርክ ሾፑ ተሳታፊ አቶ በየነ ያለው ደግሞ የአባቶቻችን ባህላዊ የዕርቀ ሰላም ስርዓት እዩተዳከመ በመሔዱ በስላማች ላይ ፈተና ተደቅኗል።ይህ ባህላዊ የዕርቀ ስላም ስርዓት እንዲጠናከር ሁሉም ባለ ድርሽ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ስጥተዋል።
የወርክሾፑ ተሳታፊ ወጣት ቤተልሔም ደግሞ ወጣቱ ትውልድ ለሀገሩ ስላም ሲል የአባቶችን ባህላዊ የዕርቅ አፈታት ስነ- በማክበርና በማገዝ ኃላነታች ልንወጣ ይገባል ስትል አስተያየትዋን ስጥታለች።


