ማኅበራችን ከዩስኤድ ኦቲአይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር በአይከል ከተማ እና በጎንደር ከተማ ዙሪያ ቀበሌዎች “ወጣቶችን ከሀይማኖት መሪዎችና ከሸምጋይ አባቶች ጋር በማቀራርብ ሰላምን መገንባት” በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ አካሄደ። ይህ የውይይት መድረክ ከጥቅምት 15-18/2014 ዓ/ም የተደረገ ሲሆን ከጎንደር ከተማና አይከል ከተሞች የተወጣጡ ወጣቶች፤የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በኤጂ ሆቴልና ሄርፋዚ ሪዞርት በአራት የመወያያ አዳራሾች በተለያዩ አጀንዳዎች ሲወያዩ ሰንብተዋል። ውይይቱ አልሞ የተነሳውም በሰላም ግንባታ የወጣቶችን ሚና ማሳደግ፤የወጣት ለወጣት ውይይቶችን ማበረታታት፤ በወጣቶች እና በእምነት ተቋማት መሪዎችና ሸምጋይ አባቶች መካከል ጠንካራ ትስስር መፍጠር፤ የጋራ ጉዳዮችን ለይቶ ለማወቅና የመፍትሄ እርምጃዎችን ለመከተል፤ የእምነት ተቋማት መሪዎችና ሸምጋይ አባቶች በወጣቶች መካከል ግጭትን ለመቀነሰ መሰረት ያደረጉ ዉይይቶችን እንዲያመቻቹ ማድረግ ናቸዉ፡፡
በሄርፋዚ ሪዞርት በነበረው የማጠቃለያ መድረክ ጥሪ የተደረገላቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሀይ፣ የከተማዋ ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ እና ሌሎች የከተማዋ የመንግስት አመራሮች ተገኝተው ማኅበራችን ግዮን ዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር ግጭቶችን ቀድሞ ለመከላከል ታዳጊ የነገ ሀገር ተረካቢዎች ላይ እያስቀመጠ ያለውን አሻራ አመስግነው በውይይቱ ለተሳተፉ ወጣቶችም አበረታች ንግግር አድርገዋል።
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማኅበር
ጥቅምት 19/2014 ዓ/ም




