ማህበራችን ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) ጎንደርና አካባቢው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ተጨማሪ ጥረት የሚጠይቁ አካባቢዎችን በመለየት የሰላም ግንባታ ስራውን የቀጠለ ሲሆን በድባ ደፈጫ ቀበሌ የነበሩ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ቀደመ ኑባሬያቸው እንዲመለሱ እና እንዲጠናክሩ ያለመ ዝግጅት አድርጓል።
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ) በጎንደር ዙሪያ ግጭት ተፈጥሮባቸው ከነበሩ ቀበሌዎች አንዱ በሆነው ድባ ደፈጫ ቀበሌ የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት በሚያሰፍን እና የቀደመውን ግንኙነት ለመመለስ ያለመ ዝግጅት አካሂዷል። በውይይቱም የማህበሩ አባላት፣ የቀበሌው አመራሮች እና የፀጥታ አካላት የተገኙ ሲሆን ከአሁን በፊት ላልተው የነበሩ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ወደ ቀደመ ኑባሬያቸው እንዲመለሱ እና የአካባቢውን ሰላም ወደ ዘላቂ መረጋጋት ለማምጣት በቁርጠኝነት የጋራ ተግባቦት መፍጠር ተችሏል። ህብረተሰቡም ብርድ እና ዝናብ ሳይበግረው ለሰላም ዘብ መሆን እና ቁርጠኝነቱን አሳይቷል።
ግዮን የዕርቀ ሰላምና ልማት ማህበር (ግዕሰልማ)
ሐምሌ 2014 ዓ.ም


